አምላክ ሰው ለመሆን ስለአፈቀረ/2/ በነቢያት አድሮ /2/ ትንቢት አናገረ በአዋጅ ተነግሮ ትንቢቱ ሲፈፀም /2/ አምላክ ተወለደ /2/ ከድንግል ማርያም ከድንግል ማርያም በለበሰው ሥጋ /2/ እኛን ወገኖቹን /2/ አለበሰን ጸጋ ነቢያት በትንቢት ጻድቃን በውዳሴ /2/ ይነጋገራሉ /2/ ከድንግለ ሙሴ ንጽህናዋን አይቶ ነውር እንደሌለባት /2/ መልአኩ ገብርኤል /2/ ትፀንሻለሽ አላት ድንግለ ሙሴ (የሙሴ ድንግል) እመቤ ችን ናት።