ምድረ ቀራንዮ ምድረ ጐልጐ /2/ መድኃኒት ክርስቶስ በአንቺ ተንገላ የዓለም መድኃኒት በአንቺ ተንገላ መስክሪ አንቺ ምድር ግዑዚቷ ስፍራ /2/ መድኃኒት ክርስቶስ ያየብሽ መከራ /2/ ደሙ እንደውሃ ሲወርድ በመስቀሉ ላይ /2/ መከራን ሲቀበል በዚያች ምድር ላይ /2/ አዝ . . . ፀሐይ ከለከለች ከመስጠት ብርሃን /2/ ለመሸፈን ብላ የአምላኝን እርቃን /2/ ሁሉን ማድረግ ሲችል ስልጣን ሲኖረው /2/ በቀራንዮ መስቀል ፍቅሩ አዋለው /2/ አዝ . . . 43 በመስቀል ላይ ሆኖ ተጠማሁ እያለ /2/ ተገርፎ ተስቅሎ ቀራንዮ ዋለ /2/ እጆቹና እግሮቹ በችንኝር ተመተው /2/ ይቅር ን አድርጎ ለዚያ ኃጢአ ቸው /2/ አዝ . . . ቸሩ መድኃኔዓለም እባክህ ማረን /2/ ደኝሞች ነንና እንዳንቀር ወድቀን /2/ በቆረስከው ሥጋ ባፈሰስከው ደም /2/ አቤቱ ተራዳን እስከ ዘለዓለም /2/ አዝ . . .