ምድር ፀዳች ሐሴት አረገች ምድር ፀዳች ከእድፍ ነፃች በክርስቶስ ደም በእውነት ጠበች /2/ ሴቶች ትንሳኤውን ሲያወሩ በደስ /2/ ሟሀ ስትመሰክር ምድር አፍዋን ከፍ /2/ የተዘጋው ዓለም ሲገለባበጥ /2/ ምን ተናገሩ አይሁድ ከፍርድ ለማምለጥ አያልቅባቸውም የእነርሱ ፈሊጥ /2/ አዝ .... መግነዙ ተገኘ ከመቃብር ወድቆ /2/ ምልክት እንዲሆን ተወላቸው አውቆ /2/ እሑድ በማለዳ መቃብሩ መከነ /2/ ሁሉም ተለውጦ ለቅሶው ደስ ሆነ /2/ አዝ .... ሁለቱ መላእክት ብርሃን የለበሱ /2/ ተነስቷል አሏቸው ሴቶች ሲደርሱ /2/ ሐዋርያት ሰምተው ዜና ትንሳኤውን /2/ አላቸው በድንገት ሰላም ለእናንተ ይሁን /2/ አዝ .... መቃብሩ መከነ መቃብሩ ባዶ ሆነ ማለት ነው።