የትንሣኤው ብርሃን የሰው ልጅ ሕይወት /2/ አዳምን መለሰው ከወጣበት ቤት /2/ እሰይ የምሥራች ደስ ይበላችሁ ሞትን ድል አድርጎ ተነሳላችሁ /2/ አዝ ያ በሙሴ ኦሪት የተነገረው /2/ ሞትን ዛሬ አጥፍቶ የተነሳው ነው /2/ አዝ .... ማርያም መግደላዊት ምንኛ ደልሽ /2/ ከሰው ሁሉ በፊት ትንሣኤን አየሽ /2/ አዝ ....