ጻድቃን ሰማዕ ት በሙሉ በአኝለ ሥጋና በአኝለ ነፍስ /2/ ያሉ ከፈጣሪ አማልደው እኛን ያስምራሉ የእግዚአብሔር ዐይኖቹ ጻድቃንን ከማየት ጆሮ−ቹም አይርቁም እነርሱን ከመስማት የጻድቅ ሰው ጸሎት ኃይልን ደርጋለች በምልጃቸው እንመን አናመን በአንዳች አዝ . . . ጊዜያዊው ፈተና ሳያሰቅቃቸው እሳትና ስለት ሳያስፈራራቸው ሰማያዊው ተስፋ ስለሚ ያቸው በመከራ ሁሉ ጸኑ በእምነ ቸው አዝ . . . ኃጥኡ ነዌ እንኳን በሲዖል እያለ ስለወንድሞቹ ምሕረት ከለመነ እናንተማ ጻድቃን በገነት ያላችሁ ምንኛ ትረዱን አምነን ስንጠራችሁ አዝ . . . ቀዝቃዛ ውኃ እንኳን በጻድቅ ሰው ስም የሚያጠጣ ቢኖር ዋጋው አይጠፋም ብሎ እንዳስተማረን ጌ በወንጌል አምነን እንፈጽመው ዋጋ ያሰጣል አዝ . . .