መልእክተ ወንጌልን በደሙ የጻፈ ስቃዩን ግሶ ችሎ ያሳለፈ በረሃብ በግርፋት በግ ካት አብዝቶ በገድል በትሩፋት ጠላትን ድል ነስቶ ንዋይ ሩይ ነው ለዓለም ያበራ ሐዋርያው ጳውሎስ ለጽድቅ የተጠራ እንቅልፉን እያጣ ሌት ተቀን ሳይ ክት የኋላውን ትቶ ተጓዘ ወደፊት በድኝም ተጠምዶ በገድል እያረሰ ከደማስቆ እስከ ሮም ቃሉን አዳረሰ አዝ . . . እውነት ለመናገር ከቶ ያላፈረ ሕዝብን ከአሕዛብ በአንድ ያስተባበረ አምላኩ እንዳይናቅ ከልቡ የተጋ ጸንቶ የተጓዘ ለምትበልጠው ጸጋ አዝ . . . በሮም አደባባይ ሰማዕት የሆነ የተዋሕዶ አርበኛ ለአምላኩ የ መነ በጣዕመ ስብከቱ ዓለምን አጣፍጦ አክሊል ተቀዳጀ ሳይ ክት ሮጦ አዝ . . .