ልቡና የሚመስጥ መዓዛ እጣኗ ሕሊናን ይገዛል ዝማሬ ድጓዋ የቅዱሳን በዓት የጸሎት ዋሻቸው ቤተ ክርስቲያን ናት አምባ መጠጊያችን አዝ የመላእክት ዜማ የአዕዋፍ ዝማሬ የሚለቀምባት የትሩፋት ፍሬ አዝ . . . ይዘምሩባ ል በአንድነት ተባብረው የሌዋዊው በትር ፀናፅል ከበሮው አዝ . . . ወራዳዋን ዓለም የናቋት በቅድሚያ የእምነት አርበኞች ያገšት በፍልሚያ አዝ . . . የገድላቸው ተዓምር መንቦግቦጊያ መቅረዝ የሰማዕ ት አክሊል የሥራቸው ደሞዝ አዝ . . . መውደቂያዬ ይሁን ከመቃብራቸው ይፈውሳልና ተረፈ አጽማቸው አዝ . . . ከኃጥአን ድንኝን መውጣቴ ነው ዛሬ የቅዱሳን በዓት ልትሆነኝ ሀገሬ አዝ . . .