ከክርስቶስ ፍቅር የሚለየኝ ማነዉ/2/ መከራ ችግር ስቃይ ወይስ መራቆት ነዉ/2/ አንፈራም አንሰጋም አንጠራጠርም/2/ እግዚአብሔር ከኛ ጋራ ይኖራል ለዘለዓለም/2/ በትጋት ተራምደን እንግባ በጠዋት/2/ በደሙ መሥርቶ ከሠራልን ቤት/2/ ከቶ የት ይገኛል እንዲህ ያለ ቤት/2/ የዉኃ ግድግዳ የደም መሠረት/2/ የዉኃ ግድግዳ የደም መሠረት/2/ ይኸዉ እዚህ አለ የአማኑኤል ቤት/2/