ንሴብሖ/2/ ለአምላከ ዕዝራ/2/ ንሴብሖ ለአምላከ ዕዝራ ለምስጋና ቀሰቀስከኝ በእኩለ ሌሊት በተመስጦ ስለፍቅርህ ልጅምር ማኅሌት ንሴብሖ ለአምላከ ዕዝራ አዝ ስመለከት ወደ ሰማይ በጨረቃ ብርሃን አስገረመኝ ከዋክብቱ ሲያወሩ ሥራህን ንሴብሖ ለአምላከ ዕዝራ አዝ አእዋፉ በማለዳ መዝሙር ሲዘምሩ በቋንቋቸዉ የአንተን ክብር በምሥጢር ሲያወሩ ንሴብሖ ለአምላከ ዕዝራ አዝ ከበሮ ሆይ ጸናጽል ሆይ ለምስጋና ተነስ በማለዳ ለጌታችን ምስጋና እናድርስ ንሴብሖ ለአምላከ ዕዝራ አዝ ኑ በእግዚአብሔር ደስ ይበለን በመንፈስ እንዘምር እልል እንበል በምስጋና ስለሁሉም ነገር ንሴብሖ ለአምላከ ዕዝራ አዝ