የዘመናት ጌታ

የዕለት የዓመት የዘመናት ጌታ
ለዚህ ላደረስከኝ ዘመኔን ሳትገታ
አቀርብልሃለሁ የክብር ሰላምታ/2/

ኑ እናመስግን ከልባችን የሰማዮን አባታችንን
ለዚህ ዕለት ለዚህ ዓመት ላደረሰን ሁላችንን

የሰዉ ልጆች እድሜ ጥንቱንም ሲጅመር
ምን ቢወጣ ቢወርድ ቢበዛ ቢደመር
አንድ ቀን አይሞላም እንደ አንተ አቆጣጠር/2/

ኑ እናመስግን ከልባችን የሰማዮን አባታችንን
ለዚህ ዕለት ለዚህ ዓመት ላደረሰን ሁላችንን

ስለዚህ አምላክ ሆይ ንዑድ ነዉ ክቡር ነዉ
ወደአንተ እንዲመለስ ቀን የሰጠኸዉ ሰዉ
ደካማ ነዉና ሰዉ እድሜ ከራበዉ/2/

ኑ እናመስግን ከልባችን የሰማዮን አባታችንን
ለዚህ ዕለት ለዚህ ዓመት ላደረሰን ሁላችንን

እጅግ አደንቃለሁ የአምላክን ጥበብ
ምድርን በአበባ ሰማዮን በኮከብ
እንዳሸበረቀ አስተዉዬ ሳስብ/2/

ኑ እናመስግን ከልባችን የሰማዮን አባታችንን
ለዚህ ዕለት ለዚህ ዓመት ላደረሰን ሁላችንን

ከንቱ ካሳለፍኩት ጊዜዬን በዋዛ
ምን ያደርግልኛል ዘመኔ ቢበዛ
ደግሞም በጠቅላላዉ ዓለምን ብገዛ/2/

ኑ እናመስግን ከልባችን የሰማዮን አባታችንን
ለዚህ ዕለት ለዚህ ዓመት ላደረሰን ሁላችንን

ወርኃ ክረምት አልፎ መስከረም ሲጠባ
ምድር በልምላሜ ስታጌጥ በአበባ
እናምናለን ለአንተ ምስጋና እንዲገባ/2/

ኑ እናመስግን ከልባችን የሰማዮን አባታችንን
ለዚህ ዕለት ለዚህ ዓመት ላደረሰን ሁላችንን

Rating

5 - of 0
4 - of 0
3 - of 0
2 - of 0
1 - of 0
Avg. Rating

0