ምሥጋና ጅመረ ብሎ ሃሌ ሉያ ማኅሌታይ ያሬድ ዘኢትዮጰያ ምሥጋና ጅመረ ብሎ ሃሌ ሉያ ይበል/3/ ሃሌ ሉያ ጥዑመ ልሳን ያሬድ/3/ ዘኢትዮጵያ ብሉይን ከሐዲስ ሐዲስን ከብሉይ አስተባብሮ ይዞ ያሬድ ማኅሌታይ ምሥጢር ተገልጾለት ከምድር እስከ ሰማይ አዝ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ምሥጢር እያስማማ ምሥጋና ጅመረ በነዚህ ከተማ ለቅድስት ሥላሴ በሦስት ዓይነት ዜማ አዝ በገና ጸናፀል ሲመታ ከበሮ ዜማዉ ሲንቆረቆር በሰዉ ልጆች ጆሮ የያሬድ ዝማሬ ያድሳል አእምሮ አዝ ምእመናን እናቅርብ ለአምላክ ምሥጋና በእዝራ መሰንቆ በዳዊት በገና ዜማዉን ከያሬድ ተምረናልና በእንተ ልደቱ ለእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ