አሁን ተገለጠ የድንግል ልዕልና ከእርሷ ተወለደ ሰማያዊ መና አምላከ አማልክት ቀዳማዊ ቃል በአንቺ ላይ አደረ ማርያም ድንግል ከሰማይ ወደ ምድር አብ ቢመለከት ምንምአላገኘም እንደ አንቺ ንጽሕት መላእክት በሰማይ እኅታችን ይሉሻል በንጽሕ በድንጋሌ እነርሱን መስለሻል