ሙታንን ያድን ዘንድ የሞትሞትን ሽሮ/2/ ወልደ አምላክ ሄደ ወደ ኋላ ታሥሮ/2/ ግርማን ለኪሩቤል ያጐናጸፋቸዉ ዘዉድን ለሱራፌል የሚያቀዳጃቸዉ ከለሜዳ ለብሶ ዋለ ከፊታቸዉ አዝ ቅዱሳን እጆቹ አዳምን የሠሩት ቅዱሳን እግሮቹ በገነት የዞሩት ተቸንክረዉ ዋሉ በጠንካራ ብረት አዝ ምን በበደለ ነዉ ምን ባደረገ ነዉ /2/ ወልድ እንደ ቀማኛ ሲገረፍ የዋለዉ አዝ አዳም በበደለ የግፍ ግፍ በሠራ ቸሩ ወልደ አምላክ ዋለ በመከራ አዝ ሁሉንም ታገሰ ሁሉን ቻለ ሆድህ ትልቁም ትንሹም ሲዘባበትብህ