እስመ ለዓለም ምሕረቱ/2 አያልቅም ብዙ ነዉ የአምላክ ቸርነቱ አመስግኑት ጌታን ሁላችሁ በአንድነት መሐሪ ነዉና ለሰዉ ልጆች ሕይወት አዝ የማይሞተዉ ሞቶ የተቀበረዉ/2 ከገሃነም እሳት እኛን ሊያድን ነዉ/2 አዝ ከማርያም የነሣዉ ያ ቅዱስ ሥጋዉ ቀራንዮ ሲዉል የሚያሳዝን ነዉ አዝ በፈጠረዉ ፍጥረት እጅግ ተሰቃይቶ ነፍሳትን አወጣ ከሲኦል ለይቶ/2 አዝ