ሞተ ስለእኛ የነገሥታት ንጉሥ የኃያላን ዳኛ ሞተ ስለኛ/2/ ጐለጐታ እስኪደርስ ስቃይ ተቀበለ ሥጋዉ ተዳከመ በመከራ ዛለ በጅራፍ ተገርፎ ደም ነጠበ ገላዉ ሞተ ስለኛ/2/ ሚካኤል ዝም አለ ተገርሞ አስተዋለ ገብርኤል ሰይፉን ወደ ምድር ጣለ ከዋክብት ደንግጠዉ ረገፉ ዛሬ መላእክት አለቀሱ ቀረና ዝማሬ ሞተ ስለኛ/2/ ዑራኤል አምላኩን በመሰቀል ላይ አየ በብርሃን ጽዋ ደሙን ተቀበለ ዕንባዉ አላቆመም ጌታዉ ሲንገላታ ተገርሞ አስተዋለ በጥፊ ሲመታ ሞተ ስለኛ/2/