የሕይወቴ መታመኛ የነፍሴ ተስፋ ጌታዬ አምላኬ መድኃኔዓለም ላመስግንህ እጠግባለሁ በውዳሴህ መላእክት በሰማያት ቅዱስ (3) አንተ ነህ እያሉ በክንፋቸው አሸብሽበው ይጠሩሃል በዝማሬያቸው(፪) ቅዱስ ዳዊት በበገና ከእሥራል ሀገር(2) በተመስጦ ወደ አርያም ዘልቆ ዘመረልህ አንተነትህን አውቆ(፪) ሕፃናትም አንተን አምነው በአህያ ተቀምጠህ ስትመጣ(2) አፍ አውጥተው አመሰገኑ ሆሣዕና በአርያም አሉ(፪) ሃሌ አለ ቅዱስ ዳዊት ጸናጽል መቋሚያ አንሥቶ(2) ምስጋናህን በልቡ ሽቶ በመንፈስህ በአንተ ተመርቶ(፪) ፈለጉንም ተከትለው ካህናት በሙሉ ቆመው(2) ይቀኛሉ ለቅዱስ ስምህ በማኅሌት በመመስገኛህ(፪) እስትንፋስም ያለው ሁሉ ያመስግንህ አንተን በእውነት (2) ከልብ ሆኖ በንጹሕ እምነት እንደ ዕዝራ እንደ ዳዊት(2)