ዜኖኩ ጽድቀከ ወነገርኩ አድኀኖተከ ከሠትኩ ቃላቲከ ለሕዝብከ ኢትዮጵያ ፪ በጸጋሁ ለመንፈስ ቅዱስ ወመሀርክዎሙ አነ ይቤ ያሬድ ካህን ፪ (ትርጉም) ጽድቅህን ነገርኩኝ አዳኝነትህን አስተማርኩ ቃላትህንም ለኢትዮጵያ ሕዝብ ገለጽኩ። እኔም በመንፈስ ቅዱስ ጸጋ አስተማርኳቸው አለ ያሬድ ካህን።