በፍጡራንና ፈጣሪ መካከል ድርሻ የተሰጠህ ሰውን ለማገልገል ተራዳኢ መልአክ ጠባቂ የእስራኤል የመላእክት አለቃ ስሙ ነው ሚካኤል አማላጀ ነው ሚካኤል ሚካኤል የ አምላክ ባለሟል ለእነ ሙሴ ለህዝበ እስራኤል ፈረዖን በእስራኤል ላይ በትዕቢት ተነሥቶ ቢከታተላቸው ጦሩን አስነሥቶ ይመራቸው ጀመር ሚካኤል በፋና ሌሊቱን በብርሃን ቀኑን በደመና አማላጀ ነው ሚካኤል ሚካኤል የ አምላክ ባለሟል ለእነ ሙሴ ለህዝበ እስራኤል ከባህር ያወጣኸው ጸጋ ዘአብን ከአረመኔው ንጉስ እግዚእ ሐሪያን ከልለህ የጠበቅህ በብዙ ተዓምራት እኛንም ጠብቀን ከበደል ከሃጢያት አማላጀ ነው ሚካኤል ሚካኤል የ አምላክ ባለሟል ለእነ ሙሴ ለህዝበ እስራኤል በአፎሚያ ላይ ሲፎክር ጠላት ፈጥነህ የደረስከው ሊቀ መላዕክት እኛንም ጠብቀን ከክፉ ከቅሰፍት ፈጥነህ ድረስልን ሁነን ረዳት አማላጀ ነው ሚካኤል ሚካኤል የ አምላክ ባለሟል ለእነ ሙሴ ለህዝበ እስራኤል መልአኩ ሚካኤል አማላጃችን እንለምንሃለን እንድትጠብቀን አምላክ በፍርድ ቀን ጻድቃንን ሲጠራ ዋስ ጠበቃ ሁነን ሚካኤል አደራ