አፌ ለምስጋና ለውዳሴ ይከፈት /2/ ድንቅ አድርጎልኛል በአስጨነቁኝ ፊት አፌ ለምስጋና ይከፈት ፊቱ ተደፍቼ ነግሬው ምስጢር ፈጥኖ ፈጸመልኝ የልቤን ነገር ድንቅ ድንቅ ነገር ለኔ እየሰራ ሰገነት አቆመኝ ክብሩን እንዳወራ ያለምኩት እንደጉም ሲጠፋብኝ በኖ ባዶነት ሲሰማኝ ይረዳኛል ፈጥኖ የአፌን ልመና ከቶ የማይረሳ ልቤ ይደሰታል ስሙን እያነሳ ምንም በሌለበት ተስፋ ሆነኝ ጌታ ምስጋና አቀረበች ነፍሴም ተደስታ አይኔ ተመልክቷል ድንቅ ነገር ደግሞ ሽባን ሲያራምድ አልጋን አሸክሞ ምስጢሬን ሳወራ ገብቼ መቅደሱ ሰማኝ በፅሞና የታመነው እርሱ መጣሁኝ ደስ ብሎኝ እኔም እንደሐና በፈጣሪዬ ፊት ለማድረስ ምስጋና