የብርሃን ጎርፍ ናት ድንግል እናታችን ከሰማይ እያበራች ደስ አለው ልባችን ፍቅርሽን ሰላምሽን ድህነት ይሁነን ፍጥረት በሙሉ/2/ ፊትሽ ይወድቃሉ ጸጋሽ ይድረሰን/2/ ይስጠን እያሉ የኔ ልብ ምን ፅድቅ አለው አንቺን ለማስተናገድ የሃጢያት ጎተራ ነው የተሞላ በስስት ኧረ እንዴት/2/ ድንግል ትኑርበት አትፀየፍም የኔን ልብ ታሰናዳዋለች ስለሃጢያቴ የኔ እናት ምልጃ ታቀርባለች ልባቸውን የዘጉ ድንግልን ለማስገባት ህሊናቸው ይመለስ እንጸልይ ለዚህ ጥፋት አምላክን ይዛ ነው የምትመጣው እርሷን ስንመልስ ጌታን ነው የምናስቀይመው