ከጌታዬ ፍቅር የሚለየኝ ማነው/2/ መከር ችግር ስቃይ ወይስ መራቆት ነው/2/ አንፈራም አንሰጋም አንጠራጠርም/2/ እግዚአብሔር ከኛ ጋራ ይኖራል ለዘለዓለም/2/ የሰማይ ቤታችን አማኑኤል የሰራው/2/ ግንቡ ንጹህ ውሃ መሰረቱ ደም ነው/2/ ሳይነጋ ተራምደን እንጓዝ በጠዋት/2/ በደሙ መስርቶ ከሰራልን ቤት/2/ የውሃ ግድግዳ የደም መሰረት/2/ ይኸው ከዚህ አለ የአማኑኤል ቤት/2/