ምን ሰማህ ዮሐንስ በማኅፀን ሳለህ/፪/ ሕፃን ሆነህ ነቢይ ለክብር የተጠራህ/2/ እንደ እንቦሳ ጥጃ ያዘለለህ ደስታ/2/ ምን ዓይነት ድምፅ ነው ምን ዓይነት ሰላምታ/፪/ ከተፈጥሮ በላይ ያሰገደህ ክብር እንዴት ቢገባህ ነው የአምላክ እናት ፍቅር/2/ ሌላ ድምጽ አልሰማም ከእንግዲህ በኋላ ለውጦኛል እና የሰላምታ ቃሏ/፪/ በረሃ ያስገባህ ለብዙ ዘመናት እንዴት ያለ ራዕይ እንዴት ያለ ብሥራት/2/ እንደ አዲስ ምስጋና ስልቱ የተዋበ ተደምጦ የማያውቅ ጭራሽ ያልታሰበ/፪/ ከሴት ከተገኙ ከደቂቀ አዳም ድንግል ስለሆነ በሕይወቱ ፍፁም/2/ ከማኅፀን ሳለ ተመርጦ በጌታ ለማዳመጥ በቃ የኪዳን ሰላምታ/2/