አዳኙ ስምህን ዘወትር ልጠራበት ቅዱስ ኃያል ህያው ክብር የምልበት ከሃጢያት የራቀ ሐኬት የሌለበት ምስጋናህን ብቻ የምናገርበት/2/ አንደበትን ስጠኝ ጌታዬ/4/ ሕይወት የሆነውን ቃልህን ሰባኪ ገናናነትህን ክብርህን ተራኪ ለንስሃ ህይወት በጎችህን ጠሪ እንደ ሐዋሪያት ፍቅርህን መስካሪ/2/ ከከሃድያን ጋር የማይተባበር ፆምና ጸሎትን የሚያዘወትር ከጽድቅ ስራ ጋር መልካም ህብረት ያለው በምድራዊ ምኞት የማይታለለው/2/ ፈተና ሲገጥመኝ በመከራ ጊዜ የሀዘን ጥላ ጋርዶን ሲከበን ትካዜ ተመስገን የሚል በችግር በደስታ ርቱዕ አንደበትን ፍጠርልን ጌታ/2/