አለቴ ነህ አንባዬ ጉልበቴ ነህ ጌታዬ/2/ በተከበበ ከተማ ከቶ አትጣለኝ ለብቻዬ/2/ እንደ ወጣ ይቅር አትበለኝ በንስሀ ቤትህ ምልሰኝ በመቅደስህ ዓለት አቁመኝ ማዕበልና ንፋስ ሳይነቅለኝ የነገን አላውቅም እጣዬን በቤትህ ጸንቼ መኖሬን አላምነውምና ክፉ ልቤን ስፈራው እኖራለሁ የመጪውን አልመካም እኔ እፈራለሁ ወድቆ ስላየሁኝ የቆመው ሰው ባልተሰበረ ልብ በመኖሬ መቆሜን አላውቅም እስከዛሬ በወደቀው ጨክኜ ፈርጄ የደካማው በደል አለ በጄ ማንም ስላልሾመኝ ፈራጅ አድርጎ ልቤን መልስልኝ ወደ በጎ