ቋንቋዬ ነሽ ድንግል መግባቢያዬ መልስ የማገኝብሽ ከጌታዬ /2/ ባንቺ ቀርቤአለሁ ከአምላኬ ፊት ቤቴ ሞልቶልኛል በበረከት /2/ በምን ስራዬ ነው በፊቱ የቆምኩት መቼ በቅቼ ነው ስሙን የጠራሁት አስታራቂ እናት አንቺን ስለሰጠኝ ስለ ቃል ኪዳንሽ አቤት ልጄ በይኝ /2/ ቅድስና ሕይወት ከኔ ተሰውሮ በውሸት በሃሜት አንደበቴ ታስሮ በእመ አምላክ ፍቅር አዲስ ሰው ሆኛለሁ እንደ መላእክቱ ይኸው እዘምራለሁ /2/ ስለ እማምላክ ብሎ ያፈረ የለም ባንቺ ያልከበረ ሰው አይገኝም እንደ ባለማዕረግ እኔም ሰው መባሌ አንቺን አግኝቼ ነው ድንግል መሰላሌ /2/ ሰላም ለኪ ብዬ ስጀምር ሰላምታን ሐሴት ይሞላዋል መላው ሰውነቴን እንደ ቅዱስ ኤፍሬም በምስጋናሽ ልጽና በእጆችሽ ያለው አምላኬ ነውና /2/