አምላከ ተክለሀይማኖት ማረን (2) አምላከ ቅዱሳን ታረቀን (2) ስለ ቃል ኪዳንህ በቁጣህ አታጥፋን ሃዋርያው ቅዱስ ተክለ ሀይማኖት የእቲሳ አንበሳ የእኔ አባት ቁጣውን አብርደው ተክለሀይማኖት በምልጃ ተነሳ የኔ አባት ቁጣውን አብርደው ተክለሀይማኖት ቤተሰብ ሆነሃል የእኔ አባት ከሰማይ ካህናት ተክለሀይማኖት ቤተሰብ ሆነሃል የእኔ አባት የስላሴን መንበር ተክለሃይማኖት ለማጠን በቅተሃል የእኔ አባት ከከርቤ ከሚአ ተክልሀይማኖት ከሰሊክም በልጧል የእኔ አባት የጻድቁ ጸሎት ተክልሀይማኖት በእግዚአብሔር ፊት ሸቷል ስለቃልኪዳንህ ተክለሃይማኖት አምላክ ይለመናል የእኔ አባት ጸሎት ሲደርስ ተክለሀይማኖት እኛን ይታረቃል የእኔ አባት ተማጽነንብሃል ተክለ ሃይማኖት ጌታ ሆይ በስሙ የእኔ አባት በጻድቁ ጸሎት ተክለሀይማኖት በሰባራ አጽሙ የእኔ አባት ኢትዮጵያን በሙሉ ተክለሃይማኖት አስተምሮ ሲመለስ የእኔ አባት አጽመ ርስቱ ሆነቸህ ተክለሀይማኖት ደብረ ሊባኖስ የእኔ አባት የጸድቁ መንፈስ ተክለሀይማኖት ከቅዱሳን ጋራ የእኔ አባት ከልባችን ገብተህ ተክለሀይማኖት ብርሀንን አበራ የእኔ አባት በጸሎት ስቁም ተክለሀይማኖት ስምህን ስጠራ የእኔ አባት ነፍሴ ተደሰተች ተክለሀይማኖት ሲርቀኝ መከራ የእኔ አባት