colormap #003366#336699#3366CC#003399#000099#0000CC#000066#006666#006699#0099CC#0066CC#0033CC#0000FF#3333FF#333399#669999#009999#33CCCC#00CCFF#0099FF#0066FF#3366FF#3333CC#666699#339966#00CC99#00FFCC#00FFFF#33CCFF#3399FF#6699FF#6666FF#6600FF#6600CC#339933#00CC66#00FF99#66FFCC#66FFFF#66CCFF#99CCFF#9999FF#9966FF#9933FF#9900FF#006600#00CC00#00FF00#66FF99#99FFCC#CCFFFF#CCCCFF#CC99FF#CC66FF#CC33FF#CC00FF#9900CC#003300#009933#33CC33#66FF66#99FF99#CCFFCC#FFFFFF#FFCCFF#FF99FF#FF66FF#FF00FF#CC00CC#660066#336600#009900#66FF33#99FF66#CCFF99#FFFFCC#FFCCCC#FF99CC#FF66CC#FF33CC#CC0099#993399#333300#669900#99FF33#CCFF66#FFFF99#FFCC99#FF9999#FF6699#FF3399#CC3399#990099#666633#99CC00#CCFF33#FFFF66#FFCC66#FF9966#FF6666#FF0066#CC6699#993366#999966#CCCC00#FFFF00#FFCC00#FF9933#FF6600#FF5050#CC0066#660033#996633#CC9900#FF9900#CC6600#FF3300#FF0000#CC0000#990033#663300#996600#CC3300#993300#990000#800000#993333

ኪዳነ ምሕረት እመቤት እመቤት

ኪዳነ ምሕረት እመቤት እመቤት ነዪልን ነዪልን ካለንበት ከሰማያት በላይ ካለው ከማደሪያሽ ዝማሬ ከመላው ከዘላለም ቤትሽ የምድር ፍጥረታት ማርያም ማርያም ሲሉሽ የቃል እናት እመቤቴ ነይ በሠረገላሽ ኪዳነ ምሕረት እመቤት እመቤት ነዪልን ነዪልን ካለንበት ከጸጥታው ወደብ ከፍቅር አውድማ ከሰላሙ መንደር ከእውነት ከተማ ሰአሊ ለነ ቅድስት ውዳሴሽ ሲሰማ ከሚካኤል ከገብርኤል ጋር ነዪልን ከራማ ኪዳነ ምሕረት እመቤት እመቤት ነዪልን ነዪልን ካለንበት ዘርፋፋው ቀሚስሽ ይውረድ ከሰማያት እንባችን ይታበስ ባንቺ አማላጅነት በጽዮን ዝማሬ ተመላች ነፍሳችን ንኢ ንኢ ንኢ እንበል እንዳባቶቻችን ኪዳነ ምሕረት እመቤት እመቤት ነዪልን ነዪልን ካለንበት ፍጥረታት ሲድኑ በአማላጅነትሽ በአማላጅነትሽ የዘለዓለም ኪዳን አማኑኤል ሰጠሸ ትውልድ ይህን አምኖ ብጽዕት ይልሻል እናቴ መመኪያዬ ምርኵዜ ሆነሻል፡፡ ኪዳነ ምሕረት እመቤት እመቤት ነዪልን ነዪልን ካለንበት የልብን ሲያዋዩሽ ሰምተሸ ዝም አትዪም ችግረኛን አይቶ ልብሽ አይጨክንም ከዐይን ጥቅሻ ፈጥነሽ ትደርሺለታለሽ ከኀዘን ከመከራ ታሳርፊዋለሽ ኪዳነ ምሕረት እመቤት እመቤት ነዪልን ነዪልን ካለንበት