የሰማእቷ ቅድስት አርሴማ ስሟ ገነነ ታምሯ ተሰማ ከፀበሏ ምህረት ፈሰሰ በቃል ኪዳኗ ፍጥረት ተፈወሰ ቅድስት አርሴማ ተመልከች ወደኛ ምልጃሽ ቃል ኪዳንሽ ይሁነን መፅናኛ የወንጌሉን ቃል በሥራ ገልፀሻል ካለም ክብር ይልቅ አምላክን መርጠሻል የሰማእቷ ቅድስት አርሴማ ስሟ ገነነ ታምሯ ተሰማ ከፀበሏ ምህረት ፈሰሰ በቃል ኪዳኗ ፍጥረት ተፈወሰ ለጣኦት ምሥል አልሰግድም ብለሽ ሰለጌታ ፍቅር እናቴ ተሰዋሽ በአርማንያ ምድር ገድልሽ አበራ ፀንተሽ በእምነትሽ ተቀበልሽ መከራ የሰማእቷ ቅድስት አርሴማ ስሟ ገነነ ታምሯ ተሰማ ከፀበሏ ምህረት ፈሰሰ በቃል ኪዳኗ ፍጥረት ተፈወሰ በአርምሞ ሆኜ አንቺን ስማፀንሽ በዋሻሽ ወድቄ አርሴማ ሆይ ስልሽ ሀዘኔን አይተሽ አፅናንተሽኛል በፍቅር ጣቶችሽ እንባዮ ታብሷል የሰማእቷ ቅድስት አርሴማ ስሟ ገነነ ታምሯ ተሰማ ከፀበሏ ምህረት ፈሰሰ በቃል ኪዳኗ ፍጥረት ተፈወሰ ማንስ አፈረ ከደጅሽ ወድቆ አየሁኝ ሲዘምር ያዘነ ስቆ አርሴማ ነይ ከፃድቃን ከተማ ለኛ ለልጆችሽ እንድትሆኚን ግርማ የሰማእቷ ቅድስት አርሴማ ስሟ ገነነ ታምሯ ተሰማ ከፀበሏ ምህረት ፈሰሰ በቃል ኪዳኗ ፍጥረት ተፈወሰ