ተመለሺ ሱላማጢስ ተመለሺ እናይሽ ዘንድ ተመለሺ ድንግል ማሪያም ተመለሺ ተመለሺ ሱላማጢስ ተመለሺ እመቤቴ ዘንድ ተመለሺ ድንግል ማሪያም ተመለሺ ኢሳይያስ ተንብዮልሽ ፈጣን ደመና ያለሽ ጌታን በጀርባሽ አዝለሽ በግብጽ በረሃ የዞርሽ የበረሃው ሙቀት ንዳድ የለሊቱ ግርማ ከባድ በአራዊቱ ድምጽ ሁካታ ልብሽ በጭንቅ ሲንገላታ ተመለሺ ሱላማጢስ ተመለሺ እናይሽ ዘንድ ተመለሺ ድንግል ማሪያም ተመለሺ ተመለሺ ሱላማጢስ ተመለሺ እመቤቴ ዘንድ ተመለሺ ድንግል ማሪያም ተመለሺ ስለ ልጅሽ ተርበሻል ጥማትንም ተጠምተሻል ድካም መንገድ እንግልቱ እንዴት ቻልሽው አዛኝቱ የልጅሽን ነፍስ የሻቱ ጠላቶቹ ስለሞቱ መሰደዱ ይበቃሻል ቅድስት አገር ይሻልሻል ተመለሺ ሱላማጢስ ተመለሺ እናይሽ ዘንድ ተመለሺ ድንግል ማሪያም ተመለሺ ተመለሺ ሱላማጢስ ተመለሺ እመቤቴ ዘንድ ተመለሺ ድንግል ማሪያም ተመለሺ በኢትዮጲያም እለፊ ደብረ ቁስቋም ላይም እረፊ ለዘላለም ከብረሽ በአርያም ንገሺ ተመለሺ ሱላማጢስ ተመለሺ እናይሽ ዘንድ ተመለሺ ድንግል ማሪያም ተመለሺ ተመለሺ ሱላማጢስ ተመለሺ እመቤቴ ዘንድ ተመለሺ ድንግል ማሪያም ተመለሺ የበደሌ ሸክም በዝቶ ብሰደድም ጽድቄ ጠፍቶ በይ መልሺኝ ለደጃፍሽ በክንዶችሽ እቅፍ አርገሽ በአለም ስጓዝ አንቺን ትቼሽ ከእኔ እርቆ ፍቅር ጣዕምሽ በበደሌ በኃጢአቴ ዛሬ እንኳን ብሸሽ ተመለስ በይኝ እመቤቴ በእናትነትሽ ተመለሺ እመቤቴ ተመለሺ በልቤ ኑሪ ተመለሺ ስለ ኃጢአቴ አትሽሺ ተመለሺ ሱላማጢስ ተመለሺ እናይሽ ዘንድ ተመለሺ ድንግል ማሪያም ተመለሺ ለአዳም ተስፋው መድኃኒቱ ድንግል ማርያም አዛኝቱ በኃዘንሽ በስደትሽ ታጥቦ ይጥራ እድፌ በእንባሽ በቃኝ ዛሬስ ተሸነፍኩኝ እናቴ ሆይ በይ መልሺኝ ፍቅር ጣዕምሽ ታትሞብኝ ዛሬ ድህነት በአንቺ እንዳገኝ ተመለሺ እመቤቴ ተመለሺ በልቤ ኑሪ ተመለሺ ስለ ኃጢአቴ አትሽሺ ተመለሺ ሱላማጢስ ተመለሺ እናይሽ ዘንድ ተመለሺ ድንግል ማሪያም ተመለሺ