የስሙ ትርጓሜ ማን እንደ እግዚአብሔር ነው የሰውን ወደ አምላክ የአምላክን ወደሰው እኛን የሚረዳን ዘወትር በምልጃው የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ነው ከጉድጓድ ተጥሎ ፍጹም ከሚያስፈራ ከተራቡ አናብስት ዳንኤልን ያዳንከው እኛንም ተራዳን ቸል አትበለን ሰይጣን በተንኮሉ ወጥመድ ሳይጥለን የስሙ ትርጓሜ ማን እንደ እግዚአብሔር ነው የሰውን ወደ አምላክ የአምላክን ወደሰው እኛን የሚረዳን ዘወትር በምልጃው የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ነው የክፉ ሰው ስራው ከፉ ሃሳብ ነውና በቅንነት መንገድ ከቶ አይሄድምና የሞቱን ደብዳቤ ለባሕራን ሰሰጠው ሚካኤል አጥፍቶ በደስታ ለወጠው የስሙ ትርጓሜ ማን እንደ እግዚአብሔር ነው የሰውን ወደ አምላክ የአምላክን ወደሰው እኛን የሚረዳን ዘወትር በምልጃው የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ነው ገና ብላቴና ሳለሁ አንድ ፍሬ ሰው ሁሉ ሲንቀኝ ምስጋናን ጀምሬ ጸጋዬን አብዝቶ የበቃኝ ለዚህ ክብር የሚካኤል አምላክ ይመስገን እግዚአብሔር