እልፍ አእላፋት ወትልፊት ቅዱሳን ንጹሃን መላዕክት ቆሙ ለአገልግሎት ጸንተው በአንድነት ቅዱስ/3/ አምላክ በማለት ኢዮር ራማ ኤረር የመላዕክት ሀገር የሀይማኖት ፍቅር የምልክት ክር እውነት የታየብሽ የመላዕክት ክብር እልፍ አእላፋት ወትልፊት ቅዱሳን ንጹሃን መላዕክት ቆሙ ለአገልግሎት ጸንተው በአንድነት ቅዱስ/3/ አምላክ በማለት አፅናን ሲል ገብርኤል በአለንበት ቦታ በሳጥናኤል ነገድ ነበረ ሁካታ ግማሹ እየካደ ቀሪው ሲያመነታ እልፍ አእላፋት ወትልፊት ቅዱሳን ንጹሃን መላዕክት ቆሙ ለአገልግሎት ጸንተው በአንድነት ቅዱስ/3/ አምላክ በማለት የሳጥናኤል ምኞት እንደ አበባ ረግፎ ሚካኤል ተሾመ በእምነት ተደግፎ ሳጥናኤል ወደቀ ጸጋውን ተገፎ እልፍ አእላፋት ወትልፊት ቅዱሳን ንጹሃን መላዕክት ቆሙ ለአገልግሎት ጸንተው በአንድነት ቅዱስ/3/ አምላክ በማለት ቅዱሳን መላዕክት በእምነት የጸናችሁ በታላቅ አክብሮት ሰላም እንበላችሁ ስግደት ዘበፀጋ እንስገድላችሁ እልፍ አእላፋት ወትልፊት ቅዱሳን ንጹሃን መላዕክት ቆሙ ለአገልግሎት ጸንተው በአንድነት ቅዱስ/3/ አምላክ በማለት