ኃይሌ ብርታቴ ክብሬ ሞገሴ/2/ የዘለዓለሙ የአብርሀሙ ሥላሴ /2/ ተመረጠች ነፍሴ አንተን ለማወደስ ከላይ ከአርያም ከሥላሴ መቅደስ በአንድነት ሦስትነት በዙፋኑ ሞልቶ የሚሳነው የለም ለሥላሴ ከቶ ኃይሌ ብርታቴ ክብሬ ሞገሴ/2/ የዘለዓለሙ የአብርሀሙ ሥላሴ /2/ ከመንገድ ዳር ልቁም የወደቀ ላንሳ የተራበ ላብላ የታመመ አልርሳ እንደ አብርሀም አርገኝ እንደ ደጉ አባት ቤቴ እንዲሞላ ባንተ በረከት ኃይሌ ብርታቴ ክብሬ ሞገሴ/2/ የዘለዓለሙ የአብርሀሙ ሥላሴ /2/ ጠፈሩን በውሃ በጥበብ የሠራ እኔስ ይገርመኛል የስላሴ ሥራ ኑና ተመልከቱ ታምራት ሲሠራ ሰዎች እልል በሉ ወላድ ሆነች ሳራ ኃይሌ ብርታቴ ክብሬ ሞገሴ/2/ የዘለዓለሙ የአብርሀሙ ሥላሴ /2/ አብ አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ወዶናል ወልድ በተዋህዶ እኛንም መስሎናል ኃይሉ ተገለጠ የመንፈስ ቅዱስ በቅዱሳን አድሮ ሲያድን ሲፈውስ ኃይሌ ብርታቴ ክብሬ ሞገሴ/2/ የዘለዓለሙ የአብርሀሙ ሥላሴ /2/