እግዚአብሔር ሆይ እወድሃለው ስለስምህ እቃጠላለሁ ፍቅርህ እኔን ይመስጠኛል እንደ እግዚአብሔር ከየት ይገኛል/2/ ዓለም ሁሉ በጠላኝ ጊዜ ስንገላታ ይዞኝ ትካዜ አንተ ከኔ አልተለየህም እግዚአብሔር ሆይ ወደር የለህም/2/ እግዚአብሔር ሆይ እወድሃለው ስለስምህ እዘምራለው ፍቅርህ እኔን ይመስጠኛል እንደ እግዚአብሔር ከየት ይገኛል/2/ ሳዖል እኔን ሲያሳድደኝ ጎልያድም ሲዝትብኝ ግርማ ሆነህ ከፊቴ የቆምክ እግዚአብሔር ሆይ ስምህ ይባረክ/2/ እግዚአብሔር ሆይ እወድሃለው ስለስምህ እዘምራለው ፍቅርህ እኔን ይመስጠኛል እንደ እግዚአብሔር ከየት ይገኛል/2/ ሞቷል ብለው ቀብረውኝ ሰዎች ምስኪን ሆኜ ሳይኖረኝ አንዳች ከመቃብር ቆፍሮ አወጣኝ አይዞህ ብሎ አምላክ አጽናናኝ/2/ እግዚአብሔር ሆይ እወድሃለው ስለስምህ እዘምራለሁ ፍቅርህ እኔን ይመስጠኛል እንደ እግዚአብሔር ከየት ይገኛል/2/ ሃሳብህን በእግዚአብሔር ላይ ጣል ለዘላለም ያበራልሃል ታማኝ አባት እርሱ ነውና ሰላም ይሁን ለሱ ምስጋና/2/