ሐና እና ኢያቄም በስዕለት ያግኙሽ(፪) ድንግል እናታችን በጣም ደስ ይበልሽ(፪) በጣም ደስ ይበልሽ ለመዳን ምክንያት የሆነችውን እናት(፪) ንጽሕት ቅድስት እያልን እናመስግናት(፪) እናመስግናት ሐና እና ኢያቄም በስዕለት ያግኙሽ(፪) ድንግል እናታችን በጣም ደስ ይበልሽ(፪) በጣም ደስ ይበልሽ ቤተ መቅደስ ኖርሽ በቅድስና(፪) እየተመገብሽ ሰማያዊ መና(፪) ሰማያዊ መና ሐና እና ኢያቄም በስዕለት ያግኙሽ(፪) ድንግል እናታችን በጣም ደስ ይበልሽ(፪) በጣም ደስ ይበልሽ ዕፁብ ነው ድንቅ ነው የአምላካችን ሥራ(፪) የሰጠን ድንግልን እንዳናይ መከራ(፪) እንዳናይ መከራ