በእንቊ ሰንፔር ወጳዝዮን ስርጉት ደብረ ገነት ዝየ አሐድር እስመ ኃረይክዋ ይቤ ኤልያስ ነቢየ ልዑል /፪/ ምድር ሰናይት እንተ ዘልፈ ይሔውጻ እግዚአብሔር ለደብረ ምሕረት ሀገሮሙ ለኤልያስ ወሊቀ መላእክት/፪/ ትርጉም፥ ሰንፔርና ጳዝዮን በተባለ እንቊ የተሸለመች ደብረ ገነትን መርጫታለሁና በእሷ አድራለሁ አለ የልዑል እግዚአብሔር ነቢይ የሆነ ኤልያስ። እለት እለት እግዚአብሔር የሚገበኛት ምርጥ የሆነች የኤልያስና የሊቀ መላእክት ሀገራቸው የምትሆን ደብረ ገነትም ያማረች ስፍራ ናት