ተገናኙ ሆነው አቻ ለአቻ /፪/ ተመርጠዋል ለቅዱስ ጋብቻ እርሷ የእርሱ እርሱም የእርሷ ብቻ ያስደስታል እንዲህ ነው ጋብቻ በተዋሕዶ በእምነታቸው ፀንተው ከንቱውን ነገር ይህችን ዓለም ንቀው እናታችን ማርያምን ይዘው ይጓዛሉ ክርስቶስን ለብሰው ተገናኙ ሆነው አቻ ለአቻ /፪/ ተመርጠዋል ለቅዱስ ጋብቻ እርሷ የእርሱ እርሱም የእርሷ ብቻ ያስደስታል እንዲህ ነው ጋብቻ ተሳፍረዋል በአንዲቱ እምነት በጥንቲቱ ጽኑ ሃይማኖት አንድ ናቸው ማንም አይለያቸው ያኑራችሁ በእምነት ጸንታችሁ ተገናኙ ሆነው አቻ ለአቻ /፪/ ተመርጠዋል ለቅዱስ ጋብቻ እርሷ የእርሱ እርሱም የእርሷ ብቻ ያስደስታል እንዲህ ነው ጋብቻ የክብር አክሊል እንድትቀዳጁ ኢየሩሳሌም ትሁን ርስታችሁ እግዚአብሔር አምላክ ፍቅርን ይስጣችሁ ተገናኙ ሆነው አቻ ለአቻ /፪/ ተመርጠዋል ለቅዱስ ጋብቻ እርሷ የእርሱ እርሱም የእርሷ ብቻ ያስደስታል እንዲህ ነው ጋብቻ