ሐመልማል /፫/ ወርቅ ልብሱ የኛ ሙሽራ ሐመልማለ ወርቅ በባቢሎን ምድር ያልተፈተለ ነው በቤተመቅደሱ ሲለብሱት ያየነው በክብር ካባው ላይ ጸጋው ተጨምሮ ሞላቸው ሞገሱ በላያቸው አድሮ ሐመልማል /፫/ ወርቅ ልብሱ የኛ ሙሽራ ሐመልማለ ወርቅ የሙሽራው ጠረን መዓዛው ይስባል በቅብዐ ሜሮን በዕጣኑ ከብሯል ያንፀባርቃሉ እንደ አልማዝ ድንጋይ በረከትን አፍስሰው ከምህረት እጁ ላይ ሐመልማል /፫/ ወርቅ ልብሱ የኛ ሙሽራ ሐመልማለ ወርቅ በዚህ ዓለም ዕንቁ አልከበረም ዘርፉ በፆም በፀሎት ነው ያማረው መርገፉ የሰው እጅ አይደለም የተጠበበት ከላይ የመጣ ነው ዕድፈት የሌለበት