ዮም ፍስሐ ኮነ /፪/ በእንተ መርዐዊት ለመርዐዊሃ ቆሟል መሠረቱ--- ፍስሐ ኮነ በእምነት ተገንብቶ--- ፍስሐ ኮነ ብርሃን ይታያል--- ፍስሐ ኮነ ቤታቸውን ሞልቶ---ፍስሐ ኮነ ዮም ፍስሐ ኮነ /፪/ በእንተ መርዐዊት ለመርዐዊሃ ተባርኳል ማዕዳቸው --- ፍስሐ ኮነ ጽዋቸውም ሞልቷል--- ፍስሐ ኮነ በድካም የዘሩት --- ፍስሐ ኮነ ዛሬ ብዙ አፍርቷል--- ፍስሐ ኮነ ዛሬ ብዙ ሆኗል--- ፍስሐ ኮነ ዮም ፍስሐ ኮነ /፪/ በእንተ መርዐዊት ለመርዐዊሃ የወንጌልን አጥር--- ፍስሐ ኮነ በዙሪያቸው ተክለው--- ፍስሐ ኮነ ቅጽራቸው ተከብሯል --- ፍስሐ ኮነ ጠላት እንዳይቀርበው--- ፍስሐ ኮነ ዮም ፍስሐ ኮነ /፪/ በእንተ መርዐዊት ለመርዐዊሃ በሥጋ ወደሙ --- ፍስሐ ኮነ ተጣምሯል ሥጋቸው--- ፍስሐ ኮነ ምለዋል በቃሉ--- ፍስሐ ኮነ ምንም ላይለያቸው--- ፍስሐ ኮነ ዮም ፍስሐ ኮነ /፪/ በእንተ መርዐዊት ለመርዐዊሃ በእምነት ሠረገላ--- ፍስሐ ኮነ ተሳፍረው ደረሱ--- ፍስሐ ኮነ በቅድስና ልብስ--- ፍስሐ ኮነ ተሹመው ሊነግሡ--- ፍስሐ ኮነ ዮም ፍስሐ ኮነ /፪/ በእንተ መርዐዊት ለመርዐዊሃ