እቴ ሙሽራዬ ሰሎሞን ያለሽ /፪/ እኔም ልበልሽ እናቴ እምአምላክ ግቢ በቤቴ ሁሉም ሰው ለራሱ ወንበር ሲዘረጋ ለክብር ሽልማት ራሱን ሲያስጠጋ ድንግል እንደ ባርያ ውሃ ተሸክመሽ ጌታን በትህትና ታገለግያለሽ ነይ በደመና /፬/ እመቤታችን ርኅርኂተ ኅሊና እቴ ሙሽራዬ ሰሎሞን ያለሽ /፪/ እኔም ልበልሽ እናቴ እምአምላክ ግቢ በቤቴ ወርቀ ዘቦ ለብሰው በቤቱ ከሞሉት በሐርና በእንቁ ከተንቆጠቆጡት በሰው ፊት ያማሩ ብዙ ሆነው ሳለ ጌታ ግን ወደደሽ እናቴ ነሽ አለ ነይ በደመና /፬/ እመቤታችን ርኅርኂተ ኅሊና እቴ ሙሽራዬ ሰሎሞን ያለሽ /፪/ እኔም ልበልሽ እናቴ እምአምላክ ግቢ በቤቴ አሳድጎ ሳለ መልአኩ መግቦ ተሸልመሽ ሳለ በዝቶልሽ ተዉቦ እጅግ በትህትና ስላገለገልሽው እንደ ኪሩብ መልአክ ጌታን ተሸከምሽው ነይ በደመና /፬/ እመቤታችን ርኅርኂተ ህሊና እቴ ሙሽራዬ ሰሎሞን ያለሽ /፪/ እኔም ልበልሽ እናቴ እምአምላክ ግቢ በቤቴ የባርያውን ውርደት ተመልክቷልና ለወለድሽው ንጉሥ ይድረሰው ምስጋና ከልብ የወጣ እንጂ ከንቱውን አይደለም ንጽሕት እንላለን እኛ ለዘለዓለም ነይ በደመና /፬/ እመቤታችን ርኅርኂተ ኅሊና እቴ ሙሽራዬ ሰሎሞን ያለሽ /፪/ እኔም ልበልሽ እናቴ እምአምላክ ግቢ በቤቴ