ይትባረክ እንደ አብርሃም አኸ ዘለዓለም /፬/ ይትባረክ እንደ አብርሃም የአካል አንድነት---- እንደ አብርሃም በቁርባን ተሳስሮአል ----- እንደ አብርሃም ከዛሬ ጀምሮ ---------- እንደ አብርሃም ሁለትነት ጠፍቷል ------ እንደ አብርሃም ይትባረክ እንደ አብርሃም አኸ ዘለዓለም /፬/ ይትባረክ እንደ አብርሃም ከአካሉ ተጣብቃ ---- እንደ አብርሃም ዘመናት የኖረች ----- እንደ አብርሃም ዘመረች በደስታ ----- እንደ አብርሃም አካሏን አገኘች ----- እንደ አብርሃም ይትባረክ እንደ አብርሃም አኸ ዘለዓለም /፬/ ይትባረክ እንደ አብርሃም ቡሩክ ነው ምንጣፉ---- እንደ አብርሃም ጸጋ የከበበው ------ እንደ አብርሃም የሙሽሮች ድንኳን --- እንደ አብርሃም አምላክ ያልተለየው --- እንደ አብርሃም ይትባረክ እንደ አብርሃም አኸ ዘለዓለም /፬/ ይትባረክ እንደ አብርሃም እልል በሉላቸው ----- እንደ አብርሃም ዛሬ ነው ሠርጋቸው --- እንደ አብርሃም የተመረጡበት ------- እንደ አብርሃም መልካም ጋብቻቸው --- እንደ አብርሃም ይትባረክ እንደ አብርሃም አኸ ዘለዓለም /፬/ ይትባረክ እንደ አብርሃም ድንግል ሆይ ባርኪልን ሙሽሮቹን ባርኪልን /፪/ የሙሽራው መልካም ፍሬ የሙሽሪት መልካም ፍሬ አምራ ደምቃ ታየች ዛሬ ይትባረክ እንደ አብርሃም አኸ ዘለዓለም /፬/ ይትባረክ እንደ አብርሃም ከአዳም አንድ አጥንት---- እንደ አብርሃም ከጎኑ ወስደህ --------- እንደ አብርሃም አጋር እንድትሆነው ----- እንደ አብርሃም ሔዋንን ሰጠህ -------- እንደ አብርሃም ሁለቱንም ባርከህ ------ እንደ አብርሃም እንደፈጠርካቸው ------ እንደ አብርሃም ዛሬም ለሙሽሮች ------ እንደ አብርሃም ሰላምን ስጣቸው ------- እንደ አብርሃም ይትባረክ እንደ አብርሃም አኸ ዘለዓለም /፬/ ይትባረክ እንደ አብርሃም መተሳሰብ ይኑር --- እንደ አብርሃም በመካከላችሁ ----- እንደ አብርሃም ሠርጎ እንዳይገባ --- እንደ አብርሃም ሰይጣን ጠላታችሁ --- እንደ አብርሃም በፆም እና ጸሎት --- እንደ አብርሃም ይታጠር ጓዳችሁ --- እንደ አብርሃም ድንግል እየመጣች --- እንደ አብርሃም እንድትባርካችሁ --- እንደ አብርሃም ይትባረክ እንደ አብርሃም አኸ ዘለዓለም /፬/ ይትባረክ እንደ አብርሃም በቃልህ ተመርተው---- እንደ አብርሃም ለዚህ ቀን ደርሰዋል --- እንደ አብርሃም በፊትህ ጋብቻን ------ እንደ አብርሃም ይኸው ፈጽመዋል ----- እንደ አብርሃም በፈሰሰው ደምህ ----- እንደ አብርሃም ሕብረት መስርተዋል --- እንደ አብርሃም በሥጋም በነፍስም ያንተ ነን ብለዋል ይትባረክ እንደ አብርሃም አኸ ዘለዓለም /፬/ ይትባረክ እንደ አብርሃም ጌታ ሆይ በህግህ---- እንደ አብርሃም በቃልህ መሠረት --- እንደ አብርሃም አንድ ሆነዋልና ---- እንደ አብርሃም በዚች ቅድስት ዕለት - እንደ አብርሃም እርሱንም እርሷንም -- እንደ አብርሃም ባርክህ ቀድሳቸው --- እንደ አብርሃም ዘለዓለማዊ ክብር --- እንደ አብርሃም ጸጋህን ስጣቸው ---- እንደ አብርሃም ይትባረክ እንደ አብርሃም አኸ ዘለዓለም /፬/ ይትባረክ እንደ አብርሃም የዲያብሎስ ተንኮል---- እንደ አብርሃም እንዳያጠምዳቸው ---- እንደ አብርሃም እመቤቴ ማርያም ----- እንደ አብርሃም ከለላ ሁኛቸው ------- እንደ አብርሃም ከዚህች ቅድስት ቤት --- እንደ አብርሃም ሁለቱም ሳይርቁ ------ እንደ አብርሃም ፅናቱን ይስጣቸው ----- እንደ አብርሃም አብረው እንዲዘልቁ ---- እንደ አብርሃም ይትባረክ እንደ አብርሃም አኸ ዘለዓለም /፬/ ይትባረክ እንደ አብርሃም