ዕፁብ ድንቅ ሥራ /፪/ በእውነት የታደለ የእግዚአብሔር ሙሽራ በእውነት የታደለች የእግዚአብሔር ሙሽራ ነፍሳችሁ በሰማይ ርግብ ትመስላለች ከመላእክት ጋራ ዛሬ ዘምራለች እልል/፪/ በሉ ክርስቲያኖች ሁሉ ያበራ ጀመረ ሙሽራው ፀዳሉ ያበራ ጀመረ ሙሽሪት ፀዳሏ ዕፁብ ድንቅ ሥራ /፪/ በእውነት የታደለ የእግዚአብሔር ሙሽራ በእውነት የታደለች የእግዚአብሔር ሙሽራ ከክርስቶስ ሰላም እንዴት ይርቃል ሰው ሥጋና ደሙን ሳይሳሳ ከሰጠው የመንፈስ ቅዱስ ህፃናት በመሆን በሥጋ ወደሙ መቀደስ አለብን ዕፁብ ድንቅ ሥራ /፪/ በእውነት የታደለ የእግዚአብሔር ሙሽራ በእውነት የታደለች የእግዚአብሔር ሙሽራ በእግዚአብሔር ተባርኮ የመኖር ምሥጢር የዘለዓለም ሕይወት ይሰጣል ፍቅር ሥጋውን ፍሪዳ ደሙን መጠጥ አርጎ ሰጥቶናል ዐማኑኤል ሕይወቱን ለውጦ