ጌታ ሆይ እባክህ እንለምንሃለን /፪/ በፍቅር በደስታ እንድንኖር አድርገን /፪/ ጌታ ሆይ እባክህ --በኃጢአት ብንወድቅም ምንም ብንበድልህ መዓትህ የራቀ ብዙ ነው ምሕረትህ ጌታ ሆይ እባክህ አንተ ኃብታችን ነህ የራስ ዘውዳችን ውስጣችን የምትኖር የማትለየን ጌታ ሆይ እባክህ እንለምንሃለን /፪/ በፍቅር በደስታ እንድንኖር አድርገን /፪/ ጌታ ሆይ እባክህ --- አንተ ካልሰራኸው ትዳር ጎጆውን በከንቱ መድከም ነው መልፋት መባዘን ጌታ ሆይ እባክህ በቅዱስ ፈቃድህ ሁሉን ትሰራለህ የጀመርከውን ቤት ታከናውናለህ ጌታ ሆይ እባክህ እንለምንሃለን /፪/ በፍቅር በደስታ እንድንኖር አድርገን /፪/ ጌታ ሆይ እባክህ --- እንድትሰጠን ለእኛ የዕለት እንጀራችንን ምግበ ሥጋንና ጌታ ሆይ እባክህ ምግበ ነፍሳችንን ከሰይጣን ፈተና ከፀብ ከክርክር አምላክ ሆይ ሠውረን ጠብቀን ዘወትር ጌታ ሆይ እባክህ እንለምንሃለን /፪/ በፍቅር በደስታ እንድንኖር አድርገን /፪/