ሙሽራዬ /፬/ በእግዚአብሔር ፈቃድ አንድ ሆነዋል ዛሬ በእመብርሃን ፈቃድ አንድ ሆነዋል ዛሬ የተሰጣቸውን መክሊት ሳይሸሽጉ በበረከት ፍሬ በቅተዋል ለሠርጉ በቃሉ ተቃኝታ ተውባ ነፍሳቸው አምረዋል ሙሽሮች ተክሊል ተቀዳጅተው ሙሽራዬ /፬/ በእግዚአብሔር ፈቃድ አንድ ሆነዋል ዛሬ በእመብርሃን ፈቃድ አንድ ሆነዋል ዛሬ ከሀገረ ሰላም ወጥተው ከመቅደሱ በረከትን አፍሰው በክብር ተነሡ በወንጌል ታሽተዋል ጣፍጠዋል በቃሉ ሆነዋል ሙሽሮች የእግዚአብሔር አካሉ ሙሽራዬ /፬/ በእግዚአብሔር ፈቃድ አንድ ሆነዋል ዛሬ በእመብርሃን ፈቃድ አንድ ሆነዋል ዛሬ በደም ተገንብቷል የቤታቸው መቃን ታጥረዋል በፍቅሩ በማይፈርሰው ኪዳን ወደመንደራቸው አቀና ንጉሡ ጠርተውታልና በሠርጉ ሳይረሱ ሙሽራዬ /፬/ በእግዚአብሔር ፈቃድ አንድ ሆነዋል ዛሬ በእመብርሃን ፈቃድ አንድ ሆነዋል ዛሬ