ገና እንዘምራለን /፬/ እንደ መላዕክቱ ብርሃንን ለብሰን ገና እንዘምራለን ወላዲት አምላክን ከፊት አስቀድመን በዳዊት በገና መሰንቆ ታጅበን ለሥላሴ ክብር ገና እንዘምራለን ገና እንዘምራለን /፬/ እንደ መላዕክቱ ብርሃንን ለብሰን ገና እንዘምራለን በምሥጋና ሥራ ከሰለጠኑት ጋር ልብን የሚያስደስት መዝሙር እየዘመርን ያልተሰማ ዜማ ያልታየ ምሥጋና ይፈልቃል አይቀርም ከእኛ ልቦና ገና እንዘምራለን /፬/ እንደ መላዕክቱ ብርሃንን ለብሰን ገና እንዘምራለን በትዕቢት ሳይሆን በታላቅ ትህትና በልዩ ተመስጦ በፍቅር ልቦና ሥራችን ይሆናል ለአምላክ ምስጋና ገና እንዘምራለን /፬/ እንደ መላዕክቱ ብርሃንን ለብሰን ገና እንዘምራለን ዳዊት በተመስጦ እርቃኑን ቢሆንም ሜልኮል በዝማሬው ብትስቅበትም አምላክ ከወደደ እንዲያመሰግነው በደስታ እንዳይዘምር ከልካዩ ሰው ማን ነው ገና እንዘምራለን /፬/ እንደ መላዕክቱ ብርሃንን ለብሰን ገና እንዘምራለን