እናመስግነው /፬/ አምላካችን ውለታው ብዙ ነው /፪/ ከኃጢአት ገደል ከሞት ቤት ጎትቶ መንግሥቱን ለሰጠን ከሲኦል አውጥቶ ዘለዓለማዊ ቤት ታላቅ ሀብት ያደለን መቼም የማይተወን ታላቅ አባት አለን እናመስግነው /፬/ አምላካችን ውለታው ብዙ ነው /፪/ ፍጡራን ቢንቁኝ መጎስቆሌን አይተው ወዳጆች ቢሸሹኝ ተስፋ ቢስ ነው ብለው እውነተኛው ረዳት አምላኬ መች ተወኝ ሁለት እጄን ይዞ ልጄ ተነስ አለኝ እናመስግነው /፬/ አምላካችን ውለታው ብዙ ነው /፪/ ሞታችንን ሞቶ ሕይወትን ላደለን ለቸሩ ክርስቶስ ምን እንከፍለዋለን ለታላቅ ውለታው ጌታ ለዋለልን በእልልታ እንዘምር በአንድነት ሆነን