አንቺን የያዘ ሰው ምን ይጎድልበታል በምልጃሽ በረከት ቤቱ ሞልቶለታል ዘር መከር ባይኖረው ጎተራው ባይሞላ ሁሉም ይሸፈናል በረድኤትሽ ጥላ /፪/ በረከትሽ ብዙ የደናግል ገንዘብ የምስኪናን እናት የርኁባን ቀለብ ለሁሉ መጋቢ ጸጋሽ የማይጎድል ስምሽ ጥዑም ምግብ ከረሀብ የሚያስጥል /፪/ አንቺን የያዘ ሰው ምን ይጎድልበታል በምልጃሽ በረከት ቤቱ ሞልቶለታል ዘር መከር ባይኖረው ጎተራው ባይሞላ ሁሉም ይሸፈናል በረድኤትሽ ጥላ /፪/ አንቺ ብትመጪ ከምስኪኗ ቤቴ እንደ መጥምቁ እናት በዛልኝ ሐሴቴ የአዲስ ኪዳን ቁርባን መንበር ጠረጴዛ ጽድቅን አሸተትን የሕይወት መዓዛ /፪/ አንቺን የያዘ ሰው ምን ይጎድልበታል በምልጃሽ በረከት ቤቱ ሞልቶለታል ዘር መከር ባይኖረው ጎተራው ባይሞላ ሁሉም ይሸፈናል በረድኤትሽ ጥላ /፪/ ልቤ ተጠራጥሮ ኪዳንሽን ካልከዳ ልመናም አልወርድም አልይዝም አኩፋዳ ሁሉን እየሞላሽ መመገብ ታውቂያለሽ ቢዝቁት የማያልቅ ጸጋና ሃብት አለሽ /፪/ አንቺን የያዘ ሰው ምን ይጎድልበታል በምልጃሽ በረከት ቤቱ ሞልቶለታል ዘር መከር ባይኖረው ጎተራው ባይሞላ ሁሉም ይሸፈናል በረድኤትሽ ጥላ /፪/ የእግዚአብሔር ማረፊያ ኮሬባዊት ዋሻ የሕይወት ውሃ ምንጭ የህግ መፍሰሻ ነበልባል ተዋሕዶሽ ሙሴ አንቺን አይቷል ጫማውን አውልቆ በፊትሽ ተደፍቷል /፪/ አንቺን የያዘ ሰው ምን ይጎድልበታል በምልጃሽ በረከት ቤቱ ሞልቶለታል ዘር መከር ባይኖረው ጎተራው ባይሞላ ሁሉም ይሸፈናል በረድኤትሽ ጥላ /፪/