ወደማደሪያው ገብቼ ልስገድ ለእግዚአብሔር ምሥጋናንም ላቅርብ ስለ ስሙ ክብር አድርጎልኛል እና አመሰግነዋለሁ በአፀደ መቅደሱ እሰግድለታለሁ በፊቱ ለመቆም ማልጄ እነሣለሁ /፪/ ወደማደሪያው ገብቼ ልስገድ ለእግዚአብሔር ምሥጋናንም ላቀርብ ስለ ስሙ ክብር በመከራዬ ቀን ሆኖኛል መከታ ቤቱ ተገኝቼ በፍፁም ደስታ የከንፈሬን ፍሬ ልሰዋ በእልልታ /፪/ ወደማደሪያው ገብቼ ልስገድ ለእግዚአብሔር ምሥጋናንም ላቀርብ ስለ ስሙ ክብር አሥር አውታር ባለው በበገና በመላእክቱ ፊት ለማቅረብ ምሥጋና የአፌንም ነገር ሰምተኸኛልና /፪/ ወደማደሪያው ገብቼ ልስገድ ለእግዚአብሔር ምሥጋናንም ላቀርብ ስለ ስሙ ክብር ለስሙ ልንበርከክ ለእርሱ እንደሚገባ ስዕለቴን ልፈፅም ላቅርብለት መባ ወደ አደባባዩ በምስጋና ልግባ ወደማደሪያው ገብቼ ልስገድ ለእግዚአብሔር ምሥጋናንም ላቀርብ ስለ ስሙ ክብር አሸበሽባለሁ ድምፄን አሰምቼ በቤተመቅደሱ ሌሊት ተገኝቼ እንደ ካህናቱ እጆቼን ዘርግቼ /፪/ ወደማደሪያው ገብቼ ልስገድ ለእግዚአብሔር ምሥጋናንም ላቀርብ ስለ ስሙ ክብር