የፍቅር እናት የሰላም /፪/ ይናፍቀኛል ስምሽን ሳልጠራው ስቀር ማርያም በሕይወቴ ውስጥ በኑሮዬ ቅደሚ ከፊት ከኋላዬ ተደላደለ ልቤ አንቺ አለሽና ከአጠገቤ የፍቅር እናት የሰላም /፪/ ይናፍቀኛል ስምሽን ሳልጠራው ስቀር ማርያም ምኞቴም ይስመር ድብቅ ሕልሜ ልለፍ ወጀቡን ተቋቁሜ የጌታዬ እናት ነሽ ኃይልን ያደርጋል ጸሎትሽ የፍቅር እናት የሰላም /፪/ ይናፍቀኛል ስምሽን ሳልጠራው ስቀር ማርያም እንዴት እቀራለሁ ከመንገድ አደራ እናቴ አስቢኝ ለሚያስጨንቀኝ ጠላት ለሚያሳድድ አትስጪኝ የፍቅር እናት የሰላም /፪/ ይናፍቀኛል ስምሽን ሳልጠራው ስቀር ማርያም ትላንትም ዛሬም አመሥጋኝ ነኝ የለም ለነገ የሚያስፈራኝ ሜዳ ይሆናል ተራራ ልጅሽ ስላለ ከእኔ ጋራ የፍቅር እናት የሰላም /፪/ ይናፍቀኛል ስምሽን ሳልጠራው ስቀር ማርያም