ዝም አትበሉ እግዚአብሔርን አመስግኑ /፪/ ቅዱስ /፭/ በሉ መላእክቱ ሁሉ ምሥጋና ጀምሩ ቅዱስ ቅዱሰ በሉ የሙሴ እኅት ማርያም ከበሮውን አንሺው በምሥጋና መዝሙር እሥራኤልን ጥሪው አምላክን እናክብር እንዘምር በእልልታ ከእኛ ጋር ይሆናል የሠራዊት ጌታ /፪/ ዝም አትበሉ እግዚአብሔርን አመስግኑ /፪/ ቅዱስ /፭/ በሉ መላእክቱ ሁሉ ምሥጋና ጀምሩ ቅዱስ ቅዱሰ በሉ ፍጥረታትም ጩኹ ሰማያት ዘምሩ ስለቅድስናው ሁላችሁ ዘምሩ ዳዊት ሆይ ተነሣ ስለ ጽዮን ዘምር ከበሮው ይመታ በገናው ይደርደር /፪/ ዝም አትበሉ እግዚአብሔርን አመስግኑ /፪/ ቅዱስ /፭/ በሉ መላእክቱ ሁሉ ምሥጋና ጀምሩ ቅዱስ ቅዱሰ በሉ ወገኖች እንዘምር ለእግዚአብሔር ክብር ውለታው ብዙ ነው ለእኛ ያለው ፍቅር ማዳኑን ያያችሁ ዘምሩ በእልልታ ለጌታ ለእግዚአብሔር ለሠራዊት ጌታ /፪/ ዝም አትበሉ እግዚአብሔርን አመስግኑ /፪/ ቅዱስ /፭/ በሉ መላእክቱ ሁሉ ምሥጋና ጀምሩ ቅዱስ ቅዱሰ በሉ ባሕሩን አቋርጦ ወንዝ ያሻገራችሁ ተራራውን ንዶ አቀለለላችሁ በአውሎ ነፋስ መሃል መንገድ አለው ጌታ ለንጉሥ ክርስቶስ እንዘምር በእልልታ /፪/ ዝም አትበሉ እግዚአብሔርን አመስግኑ /፪/ ቅዱስ /፭/ በሉ መላእክቱ ሁሉ ምሥጋና ጀምሩ ቅዱስ ቅዱሰ በሉ