አማናዊት እናት እነኋት ማርያም ለቅዱስ ዮሐንስ ተሰጠች ለዓለም ድኅነት የምታሰጥ የዘለዓለም ህይወት /፪/ የኛ ተስፋችን ናት ኪዳነ ምሕረት /፪/ ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነሥቶ ተዋሐደ አምላክ አልተለየችም በማዳኑ ስራ እናታችን ጽዮን ማርያም መጠጊያ ጥላችን /፪/ አማናዊት እናት እነኋት ማርያም ለቅዱስ ዮሐንስ ተሰጠች ለዓለም ወልዳ አሳደገች አዝላ ተሰደደች የሁላችን እናት ድንግል ተንከራታለች ከእግረ መስቀሉ ከዙፋኑ በቀኝ ቆማለች ትላንት ዛሬም ነገም ማርልኝ እያለች /፪/ አማናዊት እናት እነኋት ማርያም ለቅዱስ ዮሐንስ ተሰጠች ለዓለም